የቀድሞቹ ጀግኖች የመሰረቷቸው የኢትዮጵያ የጦር አካዳሚወች ከቅርብ ግዜ በተለይ ከአብይ አህመድ ዘመን ወዲህ የራሱን ህዝብ መጨፍጨፍ የዘወትር ስራው የሆነ የወራሪ ማምረቻ ሆነዋል።
ጀነራል ጃገማ ኬሎን፣ ጀነራል ለገሰ ተፈራን፣ ጀነራል ደምሴ ቡልቶን፣ ጀነራል ፋንታ በላይን እና ሌሎችን ለሀገር ክብር ለህዝብ ፍቅር ዋጋ የሚሰጡ መኮንኖችን ያፈሩት የጦር አካዳሚወች ዛሬ ላይ የእናቶቻቸውን መቀነት የሚፈቱ፣ ለአንድ ፀረ-ህዝብ ግለሰብ አገልጋይ በመሆን የሀገርን ህልዉና አደጋ ላይ የጣሉ፣ በጨቅላ ህፃናት እና መንቀሳቀስ በማይችሉ አዛውንቶች ላይ ጨክነው ምላጭ የሚስቡ ሞራለ-ቢሶችን እያፈሩ ነው።
ከዓመት በፊት በመርዓዊ በአንዲት ጀምበር 108 ንፀሃንን የጨፈጨፈት እነኝህ አሸባሪወች ከጦርነቱ ማግስት ጀምሮ ሜጫ ላይ ብቻ በአዛውንቶች ላይ፣ በአብነት ተማሪወች ላይ፣ በኃይማኖት አባቶች እና በአርሶ አደሮች ላይ ተከታታይ ጭፍጨፋወችን ፈፅመዋል። ከየትኛውም አካባቢ በተለዬ ሁኔታ ቢኮሎ፣ መርዓዊ፣ ዳጊ፣ ገርጨጭ፣ አማሪት እና ብራቃት የተባሉ የሜጫ ከተሞች በንፁሃን አማራወች ደም ታጥበዋል።
በአብይ አህመድ ዘመን ያልተበረዘ የሀገር ታሪክ፣ ያልተሻረ የሞራል ህግ፣ ያልተጣሰ የህሊና ተጠይቅ የለም። በዚህ ወቅት ከአብይ አህመድ ጋር መሰለፍ የለዬለት የሀገር ክህደት የሚሆነውም ለዚህ ነው። አብይን እንደ አንድ ምክንያታዊ እና ጤናማ መሪ መቀበል በሀገር ደህንነት ላይ መዘባበትም ነው።
ኢትዮጵያን በእሳት የተለኮሰች ጎጆ እስክትመስል ድረስ የጦርነት አዙሪት ውስጥ የከተተን ግለሰብ መታገል የትውልዱ ታሪካዊ ግዴታ እንደሆነ መታወቅ አለበት።
ያለምንም ድካም፤ ያለ ምርጫም ጭምር ባገኘው ቅቡልነት ላይ አፈር በመነስነስ በህዝብ ላይ ጦርነት በማወጅ ግላጭ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ያለን እቡይ ግለሰብ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር መቀበል ከባድ የህሊና እዳ ነው።
በእርግጥ አብይ አህመድም ሆነ ብልፅግና የሚባለው ቡድን ቢያንስ አማራ ክልል በሚባለው ቀጠና ውስጥ የሞት ፅዋቸውን ከተጎነጩ ቆይተዋል። በሀገር መከላከያ ስም የሚዋጋላቸው ሰራዊት የአስከሬን ሳጥናቸው ወደ መቃ’ብር እንዳይወርድ ከማዘግዬቱ በስተቀር።
አረጋ ከበደ “ሙሴወቻችን” ሲል የጠራቸው “አድማ መከላከሎችም” የብአዴንን መሞት በአይናቸው ያዩ በመሆናቸው ለሞተ ቡድን ሙሴ ሳይሆን ቀ*ብር አስፈፃሚ የሚያስፈልግ መሆኑን ስለሚያውቁ ይህንኑ ሚና እንዲወጡ በቅርቡ ድንቅ ተግባር ይከወናል። የአብይ አህመድ የሽብር ቡድንም በቅርቡ የእጁን ያገኛል።
Asres Mare Damtie