በማይናማር በተለያዩ ካምፓች የሚገኙ ከ735 በላይ ኢትዮጵያውያንም የድረሱልን ተማጽኖ እያሰሙ ይገኛሉ።

“ ካለንበት ህንጻ እንዳንወጣ ሚሊተሪዎች በሩን ዘግተው ከልክለውናል ” – ኢትዮጵያውያን በማይናማር

ማይናማር ባጋጠማት ከባድ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን 144 ዜጎቿ ህይወት ጠፍቷል732 የሚሆኑት ተጎድተዋል። ታይላንድ ባንኮክ ደግሞ እስካሁን በታወቀው 3 ሰዎች ሞተዋልማይናማር ሬክተር ስኬል 7.7 በሆነ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው የተመታችው።

በማይናማር በከፋ ስቃይ ከሚገኙ ዜጎች መካከል በመሬት መንቀጥቀጡ አንድ ኢትዮጵያዊ ጉዳት እንደደረሰበት ኢትዮጵያውያኑ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያኑ በሰጡን ቃል ምን አሉ ?

“ ኢትዮጵያዊያን በምንገኝበት ቀጠና የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ሊከሰት እንደሚችል የማስጠንቀቂያ መረጃዎች እየወጡ በመሆናቸው ከፍተኛ ስጋት ላይ ነን። 

ካለንበት ህንጻ እንዳንወጣ ደግሞ ሚሊተሪዎች በሩን ዘግተው ከልክለውናል።

ቀን ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ KK 4 ካምፕ  የነበረ ወንድማችን በአደጋው ድንጋጤ በጥድፊያ ከፎቅ ለመውረድ ሲሞክር እግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበታል።

እንደተተነበዬው ሆኖ ችግሩ ከተከሰተ ከፍተኛ ጉዳት ይደርስብናል የሚል ስጋት አለን። አሁን የሌሊት ቢሆንም በስጋት ለመተኛት የደፈረ የለም።

ብዙ ኢትዮጵያውያን በስጋት ከቤት ውጪ (ከግቢ ውስጥ) ነው ያለነው። በሀገሪቱ ኃላፊዎች ‘መሬት መንቀጥቀጡ በ24 ሰዓት ውስጥ ድጋሚ ሊከሰት ይችላል’ የሚል ማስጠንቀቂያ እየተላለፈ ነው።

ያለንባቸው ህንፃዎች ፊንሺንግ ላይ ያሉ ናቸው። የቆዬው ህንፃም ቢሆን በአደጋው ሊጎዳ ይችላል ግን አዲስ እየተሰራ ያለው ህንፃ ያለው ደግሞ ጉዳቱ ሊብስበት ይችላል።

በዛሬው አደጋ ኮሎናቸው የፈራረሱ ያለንባቸውጨህንፃዎች አሉ። የኢትዮጵያ መንግስትን ይሁንታ ነው የሚጠብቀውና ቶሎ እንዲያስወጣን በአክብሮት እንጠይቃለን ” ብለዋል።

ዛሬ በባንኮክና ማይናማር በተከተው 7.7 ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከ150 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መጎዳታቸው ተነግሯል።

በማይናማር በተለያዩ ካምፓች የሚገኙ ከ735 በላይ ኢትዮጵያውያንም የድረሱልን ተማጽኖ እያሰሙ ይገኛሉ።“ ባለንባቸው ካምፓች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ህንፃው ተሰነጣጥቋል። ካጠገባችን የተደረመሰም አለ” – ከ730 በላይ ኢትዮጵያውን በማይናማር

በማይናማር ከ730 በላይ ኢትዮጵያውያን ባሉባቸው የተለያዩ ካምፓች 7.7 የተመመዘገበ መሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ለሞት እሩብ ጉዳይ ላይ ነን። ህንፃዎቹ ተሰነጣጥቀዋል። ከኛ አጠገብ የተደረመሰም አለ። እዚህ ባለመውጣታችን ስቃያችን በዝቷል። እባካችሁ አስወጡን” ሲሉ በሀዘን ስሜት ተማጽነዋል።

BGF ካምፕ በሦስት ህንጻዎች በተከታይ 204፣ 118፣ 59 በድምሩ 381፤ KK2 PARK አካባቢ 62፣ KK4 PARK አካባቢ 37፤ በአጠቃላይ ቢዲኤፍ ካምፕ 480፣ DKBA ካምፕ 255 ኢትዮጵያውያን እንዳሉ፤ በነዚሁ በሁሉም ህንፃዎች መሬት መንቀጥቀጡ እንደተከሰተ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ?

“ዛሬ ኢትዮጵያውያን ባለንባቸው ህንጻዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። እኛ ለጊዜው ተርፈናል፤ የተጎዳም የለም።

ያለንበት ህንፃ ግን ተሰነጣጥቋል። የተደረመሰ ህንፃም አለ ካለንበት ትንሽ ራቅ ያለ። ከ40 በላይ የሥፍራው ሰራተኞች ተጎድተዋል።

ኬቢጅኤፍ ካምፕ 480፣ ዲኬቢኤ 255 ኢትዮጵያውያን አለን። በፍጥነት ወደ ታይላንድ ብሎም ኢትዮጵያ አለመጓዛችን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እየዳረገን ነው።

ተደራራቢና ጽኑ ህመም የሚሰቃዩ፣ እንዳናጣቸው እያሰጉን ያሉ ልጆች አብረውን አሉ። የጦርነቱም ድምጽ ከእለት እለት ወዳለንበት አካባቢ እየተጠጋ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻርተር ፕሌን ልኮም ቢሆን በቶሎ የምንወጣበትን ሁኔታ ካልተፈጠረ አስቸጋሪ ነው። አሁን ላይ ስጋት፣ ድብርት፣ ጭንቀት ጽኑ ህመም፣ የብዙዎቻችን ፈተና ሆኗል።

ቢዲኤፍ ካምፕ ላይ 260 ኢትዮጵያውያን አለን። የመሬት መንቀጥቀጡ እኛም ጋ ተከስቷል። ዶርም ውስጥ ነበርን ውጭ ወጣን ሲከሰት። 

እግዚአብሔር ይመስገን በዛሬው መሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት አልደርሰብን። ለቀጣዩ ግን ከሌላው ስቃያችን በተጨማሪ ይህን ከፍተኛ ስጋት ደቅኖብናል።

መንግስት ምነው እንደዚህ እከምሆን ዝም አለን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGS) በማይናማር የተከሰተውን መሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 7.7 የመዘገበው ሲሆን፣ የቻይናው የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትወርክ (CENC) ደግሞ በሬክተር ስኬል 7.9 የተመዘገበ መሆኑን አሳውቋል።