ውሸት እንደ ፖለቲካ ፕሮግራም ዓላማ ብሎ የያዘ መንግስት በምን ሞራሉ ነው አንድን ዜጋ ውሸታም ብሎ የሚከሰው? ( አርቲስት ታማኝ በየነ )

መልካም ብርቱካንስ ዋሸች!!!! የእሷን ውሸት ትተን 17ቱ ልጆች ዛሬስ የት ናቸው? ይሄ ሁሉ ባለሙያ ተሰብስቦ በአንድ ሳምንት ውስጥ ይሄን አይነት ዘጋቢ ፊልም ሲሰራ አምስት አመት ሙሉ የጠፉትን ልጆች ወላጆች አናግሮ ምነው የአምስት ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም መስራት አቃተው? ………… ወቸ ጉድ ነው እንጅ ሌላ ምን ይባላል

ሁለት ቴሌቪዥን ጣቢያ

የኢትዮጵያ መከላከያ ጸረ መረጃ ክፍል

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ቢሮ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ)

አዲስ አበባ ፖሊስ

የአማራ ክልል ፖሊስ

የሲዳማ ክልል ፖሊስ

ይሄ ሁሉ ባለሙያ የተሳተፈው ውሸትን ለማጋለጥ ነው?

የብርቱካን እውነት ውሸት ሆነ ነው የምትሉኝ ??

መልካም ብርቱካንስ ዋሸች!!!! የእሷን ውሸት ትተን 17ቱ ልጆች ዛሬስ የት ናቸው? ይሄ ሁሉ ባለሙያ ተሰብስቦ በአንድ ሳምንት ውስጥ ይሄን አይነት ዘጋቢ ፊልም ሲሰራ አምስት አመት ሙሉ የጠፉትን ልጆች ወላጆች አናግሮ ምነው የአምስት ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም መስራት አቃተው?

ብርቱካንስ አንድ ዜጋ ነች ከዋሸች በቤተሰብም በማህረሰብም ብዙ ሊያስከፍላት ይችላል፡፡ ግን ግን ውሸት እንደ ፖለቲካ ፕሮግራም ዓላማ ብሎ የያዘ መንግስት በምን ሞራሉ ነው አንድን ዜጋ ውሸታም ብሎ የሚከሰው?

በተወካዮች ምክር ቤት፣ በአለማቀፍ መድረክ፣ በቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን ማይክ በጨበጡ ቁጥር የሚዋሹ ጠ/ሚንስተር ይዞ ብርቱካንን ውሸታም ማለት ይቻላል ወይ? ይልቅ ከየት ተማርሽው? ማን አስተማረሽ ? ብዙ የጠቅላይ ሚ/ሩን ንግግር ታያለሽ ወይ? ማለት አይሻልም ነበር?

ወደፊት ሰፋ ያለ ጉዳይ ይዠ እመለስበታለሁ፡፡ ለአሁኑ ግን እነዚህን 5 መዝናኛ ውሸቶች ይመልከቱ (15) Video | Facebook