(ምንሊክ ሳልሳዊ) ፡ …… በፌክ ዶክመንተሪ ፊልም የሕግ የበላይነትን መደፍጠጥ መንግስታዊ ድንቁርና ነው …….. በፖለቲካ እርምጃዎች ሕግን በማኮላሸት እውነትን ለመሸፈን የሚደረጉ ሩጫዎች ይብልጡኑ ያጋልጣሉ፤ …….. የአብይ አሕመድ አገዛዝ በብርቱካን ጉዳይ ለምን እንደደነገጠም ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፤ ……… እውን የአብይ አገዛዝ እውነትን አፈላላጊ ቢሆን ከዶክተር አምባቸው እስከ ሃጫሉ ግድያ እና ሌሎችንም ከፍተኛ ወንጀሎች ለምን ተድበስብሰው እንዲቀሩ አደረገ ? …… ተጠቂዎችን አስሮ ወንጀለኛ ነኝ ማሰኘት ድንቁርና ነው። የብርቱካን ታሪክ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ታሪክ መሆኑን ሚሊዮኖች ያውቃሉ! ……. ኢቢኤስ የሰራሁት የብርቱካን ፕሮግራም አምኜበት ችግር እንዳሌለበት አረጋግጬ ስለሆነ የናንተን ዶክመንተሪ አላቀርብም አላስተባብልም በማለቱ በአገዛዙ ሚዲያዎች ፌክ ዶክመንተሪ ተሰራጨ፤ በኢቢኤስ እንዲቀርብ አስገዳጅ ሁኔታዎችን በመጠቀም ላይ እንደሆናችሁ ታውቋል።. ………. በየአብይ አሕመድ አገዛዝ በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከማጥራት ይልቅ ጥቃት የተፈጸመባቸውን ዜጎች ማንገላታት እና ወንጀሉን ለመደበቅ የሚሄድበት መንገድ እጅግ አሳፋሪ ነው። ……… ለዚህም ነው አብይ አሕመድ በሚያወራው የሽግግር ፍትሕ እና የምክክር ኮሚሽን ሕዝቡ እምነት ያጣው፤ …… በፌክ ዶክመንተሪ ፊልሞች ለጊዜው መሸፈን ይቻል ይሆናል። ሕወሓትም በርካታ ፌክ ዶክመንተሪዎች ሲሰራ ኖሮ በመጨረሻ ተጋልጧል። …….. የሕወሓት የበኩል ልጅ ኦሕዴድም ይህንን ደግሞ እያሳየን ነው። …… ቀሽም ድራማ በመስራት በዶክመንተሪ ውስጥ የአገዛዙን ድንጋጤ መደበቅ አይቻልም።……. መንግስታዊ ድንቁርና ሃገርን እየገደለ ሕዝብን እያጠፋ ነው። ……. የአንድ መንግስት ስራ የሕግ የበላይነትን ማስፈን እንጂ በፌክ ዶክመንተሪ ሕግን መግደል አይደለም። እውነት ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስም። #MinilikSalsawi
