አብይ አሕመድ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዕጩዎችን እንዲጠቁም ለትግራይ ህዝብ ጥሪ አቀረበ 

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዕጩዎችን እንዲጠቁም ለትግራይ ህዝብ ጥሪ ቀረበ 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ብቁ የሚሆኑ ዕጩዎችን እንዲጠቆሙ ለክልሉ ህዝብ ጥሪ አቀረቡ። ዕጩዎቹ “የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራዎች በብቃት የሚያከናውኑ” እንዲሁም “የክልሉን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ የሚችሉ መሆን” ይገባቸዋል ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ጥሪ ያቀረቡት፤ ለመላው የትግራይ ህዝብ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በዛሬው ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት ነው። በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት፤ “የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጥቆማ ጥሪ” በሚል ርዕስ የቀረበ ነው።

አብይ በዚሁ መልዕክታቸው፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሲቋቋም መሰረት ያደረገው አዋጅ ለአስተዳደሩ የሚፈቅደው የስራ ዘመን “ሁለት ዓመት ብቻ” እንደሆነ አስታውሰዋል። ሆኖም “ተጨባጭ ምክንያት ካለ” የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ ሊራዘም እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ጉዳይ ለማስረዳት በመልዕክታቸው የጠቀሱት፤ የፌደራል መንግስት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ስርዓት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅን ነው። አዋጁ “በአንድ ክልል ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊት ከተፈጸመ”፤ የፌደራል መንግስት “የክልሉን ምክር ቤት እና የክልሉን ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል በማገድ ለፌደራል መንግስቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም” ሊወሰን እንደሚችል ይደነግጋል። 

🔴 ለዝርዘሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15505/