ጌታቸው ሽፈራው ፡ አገዛዙ የጠላፊ ጠበቃ አይደለም። ራሱ አገዛዙ ጠላፊ ነው። አገዛዙ የደፋሪ ጠበቃ አይደለም። ራሱ አገዛዙ ደፋሪ ነው። ለአመታት ታፍነው የተወሰዱት ተማሪዎች ጉዳይን ሲያድበሰብስ ኖሮ አሁን ይፋ ሲወጣ ቪዲዮ በማስወረድ ወንጀልን ለመደበቅ ጥረት እያደረገ ነው። ድንገት እውነቱ ስለወጣባቸው ደንግጠው ነው።

ይህ እውነት አማራ ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ቁልጭ አድርጎ ከማሳየት ውጭ ሌላ በህዝብ መካከልም ሆነ የሚያመጣው ችግር የለም። ችግሩ ለጠላፊዎቹ ነው። ችግሩ ለደፋሪዎቹ ነው። ችግር የሚሆነው ቤተ መንግስት ሆነውም ጫካ ያሉትን ቀጥረው ለሚያሰሩት አረመኔዎች ነው። ችግሩ በሀሰት ትርክት አማራን ሲነክሱ መዋልን ፖሊሲ ላደረጉት እርጉሞች ነው። ችግሩ አማራን ማጥቃት አላማ ላደረጉ ባለጊዜዎች ነው። ችግሩ ጫካ ላይ ገዳይና ደፋሪን የፕሮጀክት ተቋራጭ አድርገው አማራን የማሰቃየት አስፈፃማዎች፣ የመቶ አመት የሀሰት ትርክት አመንዣኪዎች ነው።
የአማራ ሰቆቃ ፍንትው ያለ እውነት ሆኖ ሊደብቁት አልቻሉም። ጫካ ወስደው ከእነ እውነታቸው ቀበርናቸው ሲሉ እውነት ፈጥጦ ሲወጣ በአደባባይ ለሚሊዮኖች የደረሰውን ወደማስጠፋት ሄዱ። ምክንያቱ ጫካ ላለ ታጣቂ አዝነው አይደለም። የህዝብ ግጭት ስለሚያስነሳ አይደለም። አስበው የሰሩት ወንጀል ስለሆነ ነው። አሁንም በየቀኑ ከአውራ ጎዳና ላይ ሙሉ ተሳፋሪ ጠልፈው የሚሰሩት ይህንኑ ነው። የሀሰት ትርክት ጎርሰው ቤተ መንግስት የገቡት የአገዛዙ አካላት በየቀኑ የሚደሰቱበት የእያንዳንዱ አማራ ስቃይ ነው።
ለመደበቅ እየጣሩ ያሉት የአንድ ወቅት ክስተትን አይደለም። እየሰሩት ያለ፣ በቀጣይ በተለያየ መንገድ የሚሰሩትን ነው። ለመደበቅ እየጣሩ ያሉት የታገቱ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን በደል አይደለም። አጠቃላይ በህዝብ ላይ ያቀዱትና፣ የሰሩት፣ እየሰሩት ያለ ነው። እየደበቁት ያለው የኦነግ ወዘተ ጉዳይ አይደለም። ተስማምተው የሚሰሩት ፀረ አማራ የጋራ ዘመቻን ነው። ለመደበቅ እየሞከሩ ያሉት በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ፀረ አማራ ፍኖተ ካርታቸውን ነው።
ግን እውነት ነው! ለመደበቅ ቢጥሩት ድንገት አደባባይ ይወጣል! ያውም በራሳቸው ዩኒቨርሲቲ፣ የህክምና ተቋማት፣ በህዝብ በስፋት በሚያየው ሚዲያ!