በነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ላይ  10% አካባቢ ጭማሬ ተደረገ

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ላይ  10% አካባቢ ጭማሬ መደረጉን ገልጿል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ፣ ከዛሬ 12 ጅምሮ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን አረጋግጠዋል።

የዋጋ ጭማሬው ምንን አስመልክቶ ነው ? በምን በምን ላይ ነው ዋጋ የተጨመረው ? የተጨመረው የዋጋ መጠንስ ምን ያክል ነው ? የሚል ጥያቄ ለዳይሬክተሯ አቅርበናል።

እሳቸውም ፦

“ አጠቃላይ 10% አካባቢ ነው የተጨመረው ፤ መጨመር ከነበረበት ማለት ነው። ከ101 ብር እንግዲህ ጨማሬውን ስናየው ወደ 10 ብር ነው የሚሆነው።

ጭማሬ የተደረገው ሪፎርሙን ተከትሎ ታርጌት ያደረገው ነው። በተለይ ቤንዚን፣ ኬሮሲንና ነጭ ናፍጣ የድጎማ ስርዓት ውስጥ አሁንም ያሉ ናቸው። 

የቀሩት ቀላል ጥቀር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ ከአምና ጀምሮ በገበያ ዋጋ እየተወሰኑ የመጡ ኮሞዲቲዎች ናቸው።

የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ ከባለፍ ሦስት ወር ጀምሮ በዓለም የገበያ ዋጋ እየተመራ ይገኛል። 

ከዛሬ 12 ጀምሮ ነው ጭማሬ የተደረገው ” ብለዋል።

አሁን በተደረገው የነዳጅ ጭማሪ አንድ ሊትር ቤንዚን 112 ብር ከ67 ሳንቲም ሲገባ ፤ አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 107 ብር ከ93 ሳንቲም  ገብቷል።