ፊታውራሪ በሻሻ

ፊታውራሪ በሻሻ!

አብይ ፊታውራሪ መሸሻ አይደለንም ጉዱ ካሳ ነን አለ ። ችግሩ የመረዳት ችግር ነው። ፊቲውራሪ መሸሻ ከሌሉ ጉዱ ካሳ የለም። ፊታውራሪ መሸሻ ከሌሉ ቄስ ሞገሴም የሉም። ፊታውራሪ መሸሻ የሉም ካሉ አበጀ በለው የማንን እጅና ደጅ ሊይዝ ነው ገበሬውን እየደራጀ ያለው ?

ፊታውራሪ መሸሻ አይደለንም ያሉት ግን አበጀ በለውም ድንገት ከቦ እንዳይዛቸው በፍርሃት ነው። ባይሆን ሱሪያቸውን አውልቀው እንዳይያዙ ከፊታውራሪ ይማሩ።የጭን ገረዱንም ከወዲሁ ይንከባከቡ ። ደግሞ ዳንኤ ፊታውራሪ መሸሻ አይደሉም እርስዎ ጉዱ ካሳ ነዎት ብሏቸው ይሆናል። ዳንኤል ድሮ ድሮ እራሱ ጉዱ ካሳ ነበር ። አሁን ጉዱ ከሳ ሆኗሎ። ከስቶ መንምኖ ጥፍሩን ሲልስ ይውላል።

በእርግጥ ፋታውራሪ መሸሻን መሆን በራሱ ሌላ ተአምር የሚጠይቅ ነው። ዘር ቆጥሮ ክብር አንብሮ የየገሌ ልጅ ብሎ መፎከርን የሚጠይቅ ነው። ዝም ብሎ ፊት አውራሪ አይሆንም የፊታውራሪ ልጅ ሆኖ ማደግን ይጠይቃል።

በዚህም ተባለ በዚያ ፊታውራሪ በሻሻ ድንገት መያዝ በእርግጥ የማይቀር ነው። ፊታውራሪ በሻሻ በፈረሳቸው ወደ በሻሻ ሲባክኑ የወልቂጤ ገደል ገብተው መሞታቸው አይቀርም። ወይዘሮ ጥሩ አይነትም ወደ አርማጭሆ ሳይሆን ወደ ወሊሶ ጥሻ ሄደው ይመነኩሳሉ። ቄስ ሞገሴና ጉዱ ካሳም በፍል ውሃ ይታጠባሉ።

በዛብህና ሰብለ ወንጌልም ላይለያዩ ይገናኛሉ።

አበጀ በለው በቤቱ ይባጃል !

Bekal Alamirew