አብይ አሕመድ ነገ በፓርላማ ማብራሪያ እሰታለሁ ብሏል

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከነገ በስቲያ ሐሙስ መጋቢት 11፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት፤ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሊሰጡ ነው።

የሐሙሱ የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ፤ የፌደራል መንግስት የስድስት ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለምክር ቤት አባላት መላኩን ተከትሎ የሚካሄድ ነው።

በ57 ገጾች የቀረበው እና “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ይህ ሪፖርት፤ በዘንድሮው በጀት ዓመት የመንፈቅ ጊዜ ውስጥ የፌደራል መንግስት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስራዎች የሚዘረዝር ነው።

ሪፖርቱ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ልማት፣ በሰላም እና ደህንነት ግንባታ፣ በውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንዲሁም በፍትህ እና አስተዳደር ዘርፎች የነበሩ አፈጻጸሞችን ዳስሷል።

ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ አፈጻጸምም በሪፖርቱ ላይ ተካትቷል።

የተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሪፖርቱ ላይ ያላቸውን ጥያቄ በጽሁፍ አስገብተው ያጠናቀቁት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እንደሆነ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የፓርላማ ምንጮች ገልጸዋል። https://ethiopiainsider.com/2025/15436/