በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በታጣቂዎች የታፈኑት የአማራ ክልል ተጓዦች

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ልዩ ስሙ “አሊዶሮ መውጫ’ በተባለ ሥፍራ ታጣቂዎች ዛሬ እኩለ ቀን ላይ የአንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተሳፋሪዎችን በሙሉ አፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል ።

ታጣቂዎቹ እገታውን የፈጸሙት፣ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል ሲጓዝ በነበረ “ፈለገ ግዮን” በተሰኘ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተጓዦች ላይ እንደኾነ ምንጮች ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ አፍነው ከወሰዷቸው ተሳፋሪዎች መካከል በርካታ ሴቶች እንደሚገኙበት ምንጮች ገልጸዋል።

በዚሁ ሥፍራ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ የእገታ ወንጀሎች እንደሚፈጸሙ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገቧ አይዘነጋም።