በአፋር ክልል በሬክተር ስኬል 5.5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

በአፋር ክልል በሬክተር ስኬል 5.5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

በአፋር ክልል በሬክተር ስኬል 5.5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ እሁድ መጋቢት 7 ምሽት መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ። ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተሰማው ርዕደ መሬት፤ ከአዋሽ ከተማ በስተሰሜን 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በኢትዮጵያ ከሁለት ሳምንት ገደማ በኋላ የተመዘገበ ርዕደ መሬት ሆኗል። እሁድ የካቲት 23፤ 2017 እኩለ ለሊት አቅራቢያ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ የተከሰተው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 5.2 ሆኖ ተመዝግቦ ነበር።

በተመሳሳይ ዛሬ እሁድ ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ53 ደቂቃ ላይ የተከስተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በአካባቢው በየካቲት መጀመሪያ ገደማ ከተከሰተው በመጠን ያነሰ ቢሆንም በበርካታ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ጠንከር ያለ የንዝረት ስሜት አስከትሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15418/