የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ 13 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በሁለት ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ላይ 13 ዓመት ፅኑ እስራትና 21 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ማሳለፉን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል መረጃውን አድርሷል።
ፍርድ ቤቱ የቀድሞዉ ከንቲባ ካቀረቡት 8 የቅጣት ማቅለያዎች 4ቱን በመቀበል እና አራቱን ዉድቅ በማድረግ ነዉ የ13 ዓመት ፅኑ እስራት የፈረደባቸው።
በዚሁ በእሳቸው መዝገብ ተከሳሽ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታርኩ ታመነ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እነ 41 ሺህ ብር ፤ አቶ ታፈሰ ቱናሻ በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራትና 51 ሺህ ብር እንዲሁም አቶ ሰይፉ ሌሊሴ የተባሉ ግለሰብ እንደዚሁ በ8 ዓመት ከ5 ወር እና 76 ሺግ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።