በትግራይ የፖለቲካ ትኩሳት፤ የኤርትራ ሚና ምንድነው?
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ፤ “በትግራይ ትርምስ እናተርፋለን ከሚሉት ወገኖች አንዱ የኤርትራ መንግስት ነው” ብለዋል። በትግራይ ያሉ የተወሰኑ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች ከሻዕቢያ ጋር “ግንኙነት አላቸው” ሲሉም ወንጅለዋል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት እርሳቸውም ቢሆኑ “ከኤርትራ መንግስት ጋር ሰላም መፍጠር አለብን” በሚል እምነት “የተወሰነ እንቅስቃሴ” ያደርጉ እንደነበር አቶ ጌታቸው በዛሬው መግለጫቸው አምነዋል። በትግራይ ያሉ የተወሰኑ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች አሁን የፈጠሩት ግንኙነት ግን የክልሉን “ህልውና” “አደጋ ላይ የሚጥል” እንደሆነ አስገንዝበዋል።
አቶ ጌታቸው “ጥቂት” ግን “አደጋ መፍጠር የሚችሉ” ሲሉ የጠሯቸው አመራሮች የፈጠሩት ግንኙነት ችግር የሚያስከትለው፤ “ለትግራይ ህዝብ ማር በማዝነብ ከሚታወቁ ሰዎች ጋር ስላልሆነ ነው” ብለዋል። ከኤርትራ ጋር እየተደረገ ያለው ይህ ግንኙነት፤ የትግራይን ፖለቲካ “ከማመስ አንጻር አስተዋጽኦ የለውም ማለት አይቻልም” ሲሉም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
“የኤርትራ መንግስት ሰዎች ፍላጎት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ‘ኤርትራን ይወራል’ ብለው በሚሰጉበት ሰዓት፤ ትግራይን ማቀዝቀዣ buffer እንዲሆን ማድረግ ነው። ጠንከር ያለ አጋጣሚ ተፈጥሯል ብለው ካመኑ ደግሞ፤ ከእኛ ሰዎች ጋር ሆነው እንደገና ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ማድረግ የሚቻልበት ዕድል ካለ ማመተርም ሊሆን ይችላል” ሲሉም አቶ ጌታቸው ተደምጠዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴የኤርትራን ሚና በተመለከተ አቶ ጌታቸው የሰጡትን ማብራሪያ ለመመልከት ➡️ https://youtu.be/Vdyl5I_xm6Q