
በአዲስ አበባ የሚገኙ 20 ያህል የምዕራባዊያን ኤምባሲዎችና የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት፣ የትግራይ ሁሉም ወገኖች ውጥረትን በማስወገድ ባስቸኳይ ንግግር እንዲጀምሩ ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠይቀዋል። ኢምባሲዎቹ፣ በክልሉ እየተባባሰ የሄደውን ውጥረት በቅርበት እየተከታተሉ መኾኑን ገልጸዋል። ለፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ድጋፋቸውን የገለጡት ኢምባሲዎቹ፣ በትግራይ በድጋሚ ወደ ግጭት የመመለስ ሁኔታ እንዳይኖር አሳስበዋል። የጋራ መግለጫውን ካወጡት መካከል፣ የአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድ፣ ቤልጂዬምና አውሮፓ ኅብረት ኤምባሲዎች ይገኙበታል።