አረና ትግራይ፣ የትግራይ ነጻነት ፓርቲ እና ባይቶና፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን መዋቅሮች በማፍረስ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ለመንጠቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከኤርትራ መንግሥት ጋር በመናበብ የሚፈጸም ነው በማለት በጋራ ባወጡት መግለጫ በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራውን የሕወሓት ቡድን ከሰዋል። ፓርቲዎቹ፣ የኤርትራ መንግሥትን ጣልቃ ገብነትና የሌሎች የውጭ ኃይሎችን አፍራሽ ሚና ለማክሸፍ አፋጣኝ ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብና የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አፈራራሚዎች ባስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል። በክልሉ የተባበሰ ኹከት እንዳይፈጠርና ቀጠናዊ ቀውስ እንዳይነግስ፣ የሕግ የበላይነት መከበር እንዳለበትም ፓርቲዎቹ አሳስበዋል።