ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ላይ በየኤምባሲው በመሄድ አምባሳደሮችን አነጋገሩ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ በትግራይ እያሽቆለቆለ የመጣውን ኹኔታ መቀልበስ በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመንና አውሮፓ ኅብረት አምባሳደሮች ጋር ትናንት መወያየታቸውን አስታውቀዋል። ጌታቸው፣ ውይይቱ የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ባለድርሻዎች ዳግም በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማድረግ ባለባቸው ጥረቶች ዙሪያ ጭምር እንደኾነ በኤክስ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል። በትግራይ ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰ፣ ሥውርና አፍራሽ ዓላማ ያላቸው በርካታ የቀጠናው ኃይሎች ሊገቡበት የሚችሉበት እድል እንዳለ ጌታቸው ጠቁመዋል።