” እየተከተላችሁት ያለው መንገድ የተገኘውን ሰላም የሚያደፈርስ አገርን እና ህዝብን ለከባድ ቀውስ የሚያጋልጥ ነው !!! ” አቡነ ማትያስ

” እየተከተላችሁት ያለው መንገድ የተገኘውን ሰላም የሚያደፈርስ አገርን እና ህዝብን ለከባድ ቀውስ የሚያጋልጥ ነው !!! “

በትግራይ ክልል ሁኔታ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከወራት በፊት ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በላኩት የተግሳፅ ደብዳቤ ምንድነበር ያሉት ?

” ካህናት አበው ፣ የቤተክርስትያን ሊቃውንት ፣ ምእመናን ፣ የአገር ሽማግሌዎች የዕድሜ ባለፀጎች በሃዘን እያነቡ አካሄዳችሁን እንድታስተካክሉ ሲለምኗችሁ እና ሲመክሯችሁ ሰክናችሁ ማሰብ እና ማዳመጥ የተሰናችሁ ምክንያት ምን ይሆን ?

‘ የእኔ አካሄድ ብቻ ነው ልክ ‘ በሚል እልህ እና አስተሳሰብ የፈረሰ እንጂ የተገነባ ህዝብ እና አገር የለም።

የናንተ መለያየት አልበቃ ብሎ በአንድነት እና በመከባበር የኖረውን ህዝብ ለማራራቅ እየሄዳችሁበት ያለው ርቀት ህዝብን ለማገልገል መቆማችሁን ጥያቄ ውስጥ የሚከት የጥፋት እና የመጠፋፋት መንገድ በመሆኑ ቆም ብላችሁ አስቡ።

ይህ ሳይሆነ ከቀረ እየተከተላችሁት ያለው መንገድ የተገኘውንም ሰላም የሚያደፈርስ አገርን እና ህዝብን ለከባድ ቀውስ የሚያጋልጥ ነው።

ስለሆነም ህዝባችሁ የሚሰጣችሁ ምክር እና ተግሳፅ ተቀብላችሁ በስክነት እና በማስተዋል የህዝባችሁን ጥያቄ እንድትመልሱ አደራ እንላለን።

የተፈጠረው የሃሳብ አለመጣጣም ለመፍታት ከአቅም በላይ አይደለም። ችግሮቻችሁን በጥበብ እና በሰለጠነ አሰራር በመፍታት ጅምር ሰላሙን በማፅናት ህዝባችሁን እና አገራችሁን በልማት ለመካስ ከልብ እንድትተጉ የአባትነት ምክራችንን እናስተላልፋለን። “