ባንዳነት በባንዳዎች እየተተነተነ ነው

ምንሊክ ሳልሳዊ እንደፃፈው

ባንዳነት በባንዳዎች እየተተነተነ ነው …. አየሩን ሞልቶታል። አርበኝነት እና ባንዳነት ልዩነት አለው! ……… ራሳቸው አንሶላ እየተጋፈፉ ሌላውን አንሶላ የሚጋፈፍ አድርገው ሲያቀርቡት አያፍሩም፤ ማን ከማን ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ እንደነበር ለምን አይነግሩንም ? …… ስልጣን ላስታቀፋቸው፣ የስልጣን አባታቸው፣ የስልጣን መርዘም፣ ጦርነትን የሚናፍቁት የጦርነት ሱስ ላለበት የውሸት ቋት ለሆነ ሰው አሽከር መሆን እንደ ታላቅነት ቆጥረው የአማራን ሕዝብ ጠላቶችን ሊነግሩን ይዳዳቸዋል።

……… አብይ አሕመድ አማራን ቅቤ እየቀባው ነውን ? ……. አርበኛው አማራ ጠላቱን ያውቀዋል አራት ነጥብ ……… ሻዕቢያ እና ወያኔ የአማራ ጠላቶች ቢሆኑም ኦህዴድን ብልፅግናን ማን ወልዶ ማን አሳድጎት ማን እዚህ አደረሰው ? ……… ዛሬ ላይ አሽከር ሆነውት የሚያሳልጡለት የሚያሽካልሉለት የባንዳዎቹ ልጆች ኦሕዴድ እኮ የሻዕቢያ እና የወያኔ የበኩር ልጅ በሻዕቢያ እና በወያኔ አስተሳሰብ ያውም በሰፋ መልኩ የአማራ ጠላት ሆኖ ምን እየሰራ እንደሆነ እኮ እያየን ነው። ……… ባንዳዎቹ ስለ ባንዳነት ተንትነው ሊያሳዩን የሚሞክሩት እኮ ባንዳ የሆነውን የብልፅግ ናን ጸሎት ነው።

………… አስመሳይነት፣ ያልሆኑትን መለፍለፍ፣ የፖለቲካ ማባበል፣ ከትላንት ታሪክ አለመማር ፣ አደርባይነት፣ የፖለቲካ መሽኮርመም፣ አቋም አልባነት፣ በሽቆ ማብሸቅ ፣ ማድበስበስ፣ ማዘናጋት፣ ሕይወት አልባ የፖለቲካ ክሕደት፣እያባበሉ አድፍጦ መግደል፣ ለስልጣን መስገብገብና ያለሙትን ማጣት ወዘተረፈ እርግማን ነው ።

…….. በነፈሰበት የሚነፍሱ ትላንት ያሉትን ረስተው ዛሬ ሌላ ሊነግሩን የሚፈልጉ ነገ ደግሞ እኛ መስለው የሊመጡት የባንዳ አሽከር ሆነው ስለ ባንዳነት አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩ ርካሽ አደርባዮች የተረገሙ ናቸው። ጥይት በተተኮሰበት ማጨብጨብ ጤነኝነት አይደለም………… አደርባይነት እርግማን ነው …….. #MinilikSalsawi