በደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት ” እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር ” ሲል ውድቅ አደረገው። 

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ” እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር ” ሲል ውድቅ አደረገው። 

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ” አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር ” ሲል አጣጥሏቸዋል።

ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ላይ የወሰዱት ጊዚያዊ የእግድ እርምጃ አስመልክቶ ሌሊት መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ፕሬዜዳንቱ የወሰዱት እርምጃ ” በሌለ ስልጣናቸው የወሰዱት የማይተገበር ” ሲል በፅኑ ተቃውሞታል።

” እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር ” ሲል ውድቅ ያደረገው መግለጫው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳን ” ከስልጣቸው የኋላፊነት ቦታ ማንሳቱን ” አስታውሰዋል። 

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ” አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር ” ሲልም አጣጥሏቸዋል።

” የእግድ እርምጃውን የተደራጀ ሰራዊት ለማፍረስ ሲደረገው የቆየው ተንኮል አካል ነው ” ያለ ሲሆን ” እርምጃው አደገኛ ውጤት የሚያስከትል ነው ” ሲል አስጠንቅቋል። 

” መሰረተ ቢስ ” ሲል የገለፀው የሦስቱ ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ጊዚያዊ እግድ ፤ የሰራዊት አባላትና ህዝቡ እንዳይቀበሉት የሚል ጥሪም አስተላልፏል።