ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሰራዊት አዛዦች በአቶ ጌታቸው ረዳ ከስራ ታገዱ

ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሰራዊት አዛዦች በአቶ ጌታቸው ረዳ ከስራ ታገዱ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ በሶስት የትግራይ ሰራዊት አዛዦች ላይ የስራ እግድ ውሳኔ አስተላለፉ። ፕሬዝዳንቱ ከዛሬ ሰኞ መጋቢት 1፤ 2017 ጀምሮ ከስራ ያገዷቸው ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፤ ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ሜጀር ጄነራ ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጄነራል ምግበይ ኃይለ ናቸው።

አቶ ጌታቸው የእግድ ውሳኔውን ለጦር አዛዦቹ ያሳወቁት፤ ለእያንዳንዳቸው በዛሬው ዕለት በጻፉት ደብዳቤ ነው። ፕሬዝዳንቱ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትላቸው የሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደንም ጉዳዩን እንዲያውቁት በደብዳቤው ግልባጭ ላይ አካትተዋቸዋል።

ደብዳቤው የሰላም እና ጸጥታ ካቤኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ከሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ በተጨማሪ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮም ግልባጭ ተደርጓል። ተመሳሳይ ይዘት ያለው የአቶ ጌታቸው ደብዳቤ፤ ቅድሚያ የሰጠው በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት ያለውን ሁኔታ መግለጽን ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15324/