ሳልሳይ ወያነ፣ ከአንድ የሕወሓት አንጃ ጋር ትስስር ያላቸው የትግራይ ጸጥታ ኃይል አዛዦች ሕጋዊነት የሌለው አስቸኳይ ወታደራዊ ሕግ በማውጣት ሕዝብን እያሸበሩ ነው በማለት ከሷል።
ፓርቲው፣ የጸጥታ ኃይል አዛዦች የኾኑት ወታደራዊ መኮንኖች ሕጉን በተቃወሙ ወጣቶች ላይ ጭካኔ የተሞላበት የአፈና ድርጊት እየፈጸሙ ይገኛሉ በማለት አውግዟል።
ፓርቲው፣ በሕወሓት-መራሽነት ትግራይ ባኹኑ ወቅት እየገባችበት ያለውን ውጥንቅጥ መግታት ያስፈልጋል ብሏል።
በትግራይ ኋላቀር የፖለቲካ ጥፋቶች እየተፈጸሙ የሚገኙት በኹሉም የሕወሓት አመራሮችና ካድሬዎቻቸው እንዲኹም በክልሉ የጸጥታ ኃይል አዛዦች አማካኝነት እንደኾነ ፓርቲው ጠቅሷል።
ፓርቲው፣ መላው የትግራይ ሕዝብ ከተጻራሪ ቡድኖች አደገኛና ኋላ ቀር ፖለቲካ እንዲጠብቅና ከሳልሳይ ወያነ ጎን እንዲቆምም ጥሪ አድርጓል።