” እዚህ ያለነው ወደ 70 ኢትዮጵያውያን ነን ፤ ያለንበት ሁኔታ አስከፊ ነው ፤ ያናገረን አንድም አካል የለም ” – ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

በማይናማር / ማይዋዲ KK2 የሚባለው ስፍራ የሚገኙ በቁጥር 70 የሚሆኑ ወጣቶች ከቦታው የሚያስወጣቸውን አጥተው ጭንቀት ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል።
ያሉበት ቦታ በማይናማር ወታደራዊ ሰዎች እየተጠበቀ እንዳለ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ” እኛ በጣም አስከፊ ሁኔታ ላይ ነን። 70 እንሆናለን። ማንም መጥቶ የጠየቀን የለም። መቼ እንደምንወጣም አናውቅም። ሁሉ ነገር ጨልሞብናል ” ብለዋል።
” የሚሰጠን ምግብ የማይበላ ነው። ማደሪያ የለንም እንጨት ላይ ነው የምንተኛው ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ለመናገር ይከብዳል ስቃይ ላይ ነን ” ሲሉ ገልጸዋል።
” ባለፈው አንድ ወንድማችን በጣም ታሞ በስንት መከራ ነው ህይወት የዘራው ” ሲሉ አክለዋል።
” ያሉትን የMilitary ሰዎች ጠይቀናቸው ነበር አብረውን ካሉት ውስጥ ‘ የህንድ መንግሥት ዜጎቹን ለመውሰድ accept ስላደረገ እነሱ ይወጣሉ በእናተ በኩል ምንም ምላሽ የለም ‘ ብለውናል ” ሲሉ ገልጸዋል።
” ቢያንስ ትወጣላችሁ የሚለን የለ ወይ ስለኛ የሚናገር የለም እባካችሁ ስቃያችንን ስሙን ” ሲሉ ተማፅነዋል።

” ህንዶቹ ነገ እና ከነገ ወዲያ ይወጣሉ ዛሬ እየተዘጋጁ ነው ከኛ ሀገር በኩል ያናገረን የለም በጣም ተጨንቀናል ” ብለዋል።
እኚህ ወጣቶች ህይወትን ለማሸነፍ ሲሉ ታይላንድ ተብለው ወደ ማይናማር በግዳጅ የተወሰዱና በዛም በማፊያዎች ስንትና ስንት ስቃይ ያዩ ሲሆን ከዛ ስፍራው እንዲወጡ ከተደረጉ በኃላ አሁን ደሞ ሌላ ስቃይ እያዩ እንደሆነ አመልክተዋል።