የሳሙኤል አወቀ 9ኛ ክ/ጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ ተቆጣጥሮ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች በማህበረሰቡ ተመርጠው ህዝብን ለሚያስተዳድሩ ጊዚያዊ የቀበሌ አስተዳደሮች የእውቅናና የሰርተፍኬት ሽልማት ሰጧል

ከአማራ ፋኖ በጎጃም በየደረጃው የሚወርዱ አስተዳደራዊ መመሪያዎችን ተቀብለው ከብርጌዱ ጋር በመቀናጀት በግንባር ቀደምነት ሲያስፈፅሙና ሲተገብሩ የነበሩት የዛሬ ተሸላሚዎች ባስመዘገቡት የላቀ ውጤት ተመርጠው እውቅና መሰጠታቸውን የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ሰብሳቢ ፋኖ አለማየሁ ታምር ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት አቢዬቱን ምክንያት በማድረግ የተነሱ ዘራፊዎችንና ወንበዴዎቹን በቀበሌ አስተዳደሩ በኩል በተደረገ ማጣራትና፣በማህበረሰቡ ጥያቄ መሰረት፣ በቀጠናው በተወሰደው ሰፊ የህግ ማስከበር ዘመቻ ችግሮችን መቆጣር መቻሉ እንዳስደሰታቸው የቀበሌ አስተዳደሮች ገልፀዋል ።
የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት ፣የህብረተሰቡን የፀጥታ ችግር፣አስተዳደራዊና የፍትህ ጥያቄዎችን በቀበሌ መዋቅሩ መፍታት በመቻላቸው ለዚህ ታሪካዊ እውቅና እንደበቁም ተሸላሚዎች ለሚዲያ ክፍላችን ተናግረዋል።
የብልፅግና መዋቅራዊ ስርዓት ከፈራረሰ በኋላ ህዝቡን እያስተዳደረ የሚገኘው የአማራ ፋኖ በጎጃም በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ጊዜያዊ አስተዳደር በማዋቀር ህዝቡን ወጥ በሆነ አሰራርና መመሪያ እያስተዳደረ ከፍ ወዳለ ተቋማዊ እድገት እየተምዘገዘገ መሆኑን የአባይ ሸለቆ ብርጌድ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል ተብሏል።
በዕለቱ በነበረው ሰፋ ያለ የውውይት መድረክ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም በቀበሌ አስተዳደሮችና የብርጌድ አመራሮች ለተሳታፊዎች ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን አንኳር ችግሮችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል።