ሱዳን፣ በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ላይ በዓለማቀፉ የተመድ ፍርድ ቤት ክስ መስርታለች።

ሱዳን፣ በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ላይ በዓለማቀፉ የተመድ ፍርድ ቤት ክስ መስርታለች።

ሱዳን ክሱን የመሠረተችው፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን ጦር መሳሪያ በማስታጠቅና በገንዘብ በመደገፍ ዓለማቀፉን የዘር ማጥፋት ወንጀል ድንጋጌ ጥሳለች በማለት ነው።

ሱዳን፣ ፈጥኖ ደራሹ ኃይልና አጋሮቹ በዳርፉር ግዛቶች በማሳሊት ጎሳ አባላት ላይ የዘር ማጥፋት፣ የግድያ፣ የአስገድዶ መድፈርና የግዳጅ ማፈናቀልን ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል በማለት በክሱ ላይ ጠቅሳለች።

ኢምሬቶች ግን ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ እንዲያደርገው እንደምትጠይቅ ክሱን ተከትሎ ባወጣችው መግለጫ ገልጣለች።

ኢምሬቶች፣ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ይህን ክስ የመሠረተው፣ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎች አቅጣጫ ለማሳት ሲል ነው በማለት ክሱን አጣጥለዋለች።