የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ለተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት ለኢትዮጵያዊያን እርዳታ ፈላጊዎች 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።
ቢሮው፣ በአማራ ክልል እና በምዕራብ ኦሮሚያ የሚካሄዱ ግጭቶች እንዲሁም ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተትና ተደጋጋሚ በሽታዎች የአገሪቱን የሰብዓዊ ኹኔታ እንዳባባሱት ገልጧል።
በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ የጾታ ጥቃት፣ የንብረት ውድመትና የግዳጅ ማፈናቀል ትልቅ ችግር ሆነው ቀጥለዋል ተብሏል።
የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው ድርቅ መሰል ሁኔታ በደቡባዊና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውሃና የምግብ እጥረት ማስከተሉንና ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ የሚጠበቀው ዝናብም ተስፋ ሰጭ እንደማይሆን ቢሮው ጠቅሷል።