እናት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ እና ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፣ ኦፌኮ እና ኦነግ በቅርቡ ያወጡት መግለጫ “እሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ” ያህል ይቆጠራል በማለት ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ ተቃውመውታል።
ኦፌኮ እና ኦነግ በኦሮሚያ ክልል ለማቋቋም ያሰቡት የሽግግር መንግሥት አገሪቱን ይበልጥ የሚያመሠቃቅልና ችግሮችን የሚያባብስ እንጂ መፍትሄ እንደማያመጣ ገልጸዋል።
ፓርቲዎቹ፣ ውሳኔው በአገር ፍርስራሽ ላይ የራስን ጎጆ ለመቀለስ ያለመ፣ ኢ-ሕገ መንግሥታዊና ኢ-ሞራላዊ ነው ብለዋል። መተከልን፣ ወሎን፣ ድሬደዋን፣ ሐረርንና ሞያሌን ወደ ኦሮሚያ ለማጠቃለል መፈለግ፣ ሌሎች ክልሎች በግጭትና በኢኮኖሚ በተዳከሙበት ወቅት “ወረራ ከመፈጸም” ተለይቶ እንደማይታይም ፓርቲዎቹ ጠቅሰዋል።
የኦፌኮ እና ኦነግ ውሳኔ፣ አገሪቱን በበርካታ አሥርት ዓመታት ወደኋላ የሚመልስ እንደሆነም ፓርቲዎቹ አጽንዖት ሠጥተዋል።