ከኢትዮጵያ የወጡ ፍልሰተኞች ብዛት በ27 በመቶ ጨመረ

የምሥራቁ መስመር ተብሎ በሚታወቀው ከሱማሊያና ጅቡቲ ወደ የመን በሚወስደው የፍልሰት መስመር በኩል የሚጓዙ ፍልሰተኞች ቁጥር ባለፉት ሁለት ዓመታት በ13 በመቶ መጨመሩን ዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት አስታውቋል።

በተጠቀሰው ዓመት በዚህ መስመር በኩል ከኢትዮጵያ የወጡ ፍልሰተኞች ብዛት በ27 በመቶ ጨምሮ ቁጥሩ ከ234 ሺሕ በላይ መድረሱን የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል።

በዚሁ ዓመት በመስመሩ ከተጓዙ ፍልሰተኞች መካከል 96 በመቶዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው ተብሏል።

በተጠቀሰው ዓመት 462 ፍልሰተኞች በጀልባ መስጠም እንደሞቱም ድርጅቱ ጠቅሷል። ባለፉት ወራት ከሳዑዲ ዓረቢያ ከተመለሱት ፍልሰተኞች መካከል፣ 35 በመቶዎቹ ወደ አማራ ክልል፣ 30 በመቶዎቹ ወደ ትግራይ እና 29 በመቶዎቹ ወደ ኦሮሚያ ሂደዋል ተብሏል።