ኦሊሴጎን ኦባሳንጆን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ አገራት የቀድሞ ፕሬዝደንቶች፣ የእዳ ጫና ላለባቸው አገሮች አዲስ ዓለማቀፍ የእዳ ቅነሳ ማዕቀፍ እንዲቀረጽ ጠይቀዋል።
አዲሱ የእዳ ቅነሳ ዓለማቀፍ ማዕቀፉ፣ ኹሉም ዓለማቀፍ አበዳሪዎች ከፍተኛ የዕዳ ጫና ላለባቸው አገሮች በጠቅላላው ባንድ ጊዜ የዕዳ ሽግሽግ እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ነው።
የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች፣ አዲሱ ማዕቀፍ ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች የያዟቸውን ቦንዶችና የአበዳሪዎችን ብድሮች በሙሉ የሚያሸጋሽግና የአፍሪካ አገራትን ጨምሮ ከፍተኛ የውጭ ዕዳ የተጫናቸውን አገራት የሚያቅፍ እንዲኾን ጥሪ አድርገዋል።
የቀድሞዎቹ መሪዎች ይህን ሃሳብ ያቀረቡት፣ በቡድን-20 ሥር ለዓመታት ሲሠራበት የቆየው ‘ኮመን ፍሬምወርክ’ የተሰኘው የዕዳ ቅነሳ ማዕቀፍ የዕዳ ጫና ያለባቸውን አብዛኞቹን አገራት ተጠቃሚ አላደረገም በማለት ነው።
በ’ኮመን ፍሬምወርክ’ ሥር የዕዳ ሽግሽግ ሲደረግ የቆየው፣ የእያንዳንዱ ተበዳሪ አገር የውጭ ብድር ኹኔታ እየታየ በተናጥል ነው።