በጋምቤላ ክልል፣ በኮሌራ ወረርሽኝ እስካኹን የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ከክልሉ የጤና ቢሮ መስማቱን ጠቅሶ ዶይቸቨለ ዘግቧል።
ወረርሽኙ በጋምቤላ ከተማ፣ በጋምቤላ ወረዳ እና በሦስት የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ መከሰቱንና እስካኹን በክልሉ በጠቅላላ ከ300 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡
በሽታው በመጀመሪያ ባለፈው ሳምንት የተከሰተው በኑዌር ዞን የደቡብ ሱዳን አጎራባች በኾኑ አራት ወረዳዎች ሲኾን፣ በሽታው በተለይ ዋንቱዋ በተባለ ወረዳ ባኹኑ ወቅት በስፋት ተሠራጭቷል ተብሏል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ፣ በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሕክምና ማዕከላትን አቋቁሞ ለታማሚዎች የሕክምና አገልግሎት እየሠጠ መኾኑን ገልጧል።