በአማራ ክልል አብይ አሕመድ በፈፀመው የድሮን ጥቃት 1 ሰዎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ሐሙስ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሐሙስ’ለት በአራት ቤቶች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 16 ሰዎች እንደተገደሉ መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

በጥቃቱ ሌሎች 10 ሰዎች መቁሰላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦችና የዓይን እማኞች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በሦስት ሱቆችና ሻይ ቤት ላይ እንደኾነ መረዳቱን የገለጠው ዘገባው፣ ተጎጂዎቹ መንገድ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ሕጻናት፣ ገበያተኞችና ሻይ በመጠጣት የነበሩ ሰዎች መኾናቸውንም አመልክቷል።

አንድ የጤና ባለሙያ፣ በጥቃቱ 12 ሰዎች ቆስለው ባቅራቢያ ወደሚገኝ የግል ክሊኒክ ለሕክምና መግባታቸውንና ኹለት ታዳጊዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው እንዳለፈ ገልጸዋል ተብሏል።