የኬኒያ ባለስልጣኖች በናይሮቢ ኢትዮጵያውያንን አሰሩ

የኬኒያ ባለስልጣኖች በናይሮቢ ኢትዮጵያውያንን አሰሩ

በናይሮቢ ኬኒያ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት የሆኑ ኢትዮጵያውያን የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ያደረጉትን ስብሰባ የኬኒያ ፖሊሶች ከመበተናቸው ሌላ 40 የሚሆኑትን ህገ ወጥ ናችሁ በሚል ያሰረ መሆኑ ታውቋል። ፖሊስ ኢትዮጵያውያኑ ስብሰባውን ያደረጉት ያለፈቃድ ነው በማለት ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን በኢትዮጵያውኑ በኩል ግን ፈቃድ እንደነበራቸውና በህጉ መሰረት የሚከፈለውን ሶስት ሺ የኪኒያ ሽሊንግ የከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የኬኒያ መንግስት በተደገጋሚ ኢትዮጵያውያንን እየያዘ ለወያኔ አገዛዝ አሳልፎ መስጠቱ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህን ወገኖች ሊያስረክብ ይችላል የሚል ስጋት አለ።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE