በጎንደር ከተማ “ቅዳሜ ገበያ” በጅምላ ወደመ:: (Video)

Abdurehim Ahmed's photo.
Abdurehim Ahmed's photo.

በትላንትናው እለት ምሽት አራት ተኩል ጀምሮ የተቃጠለው በርካታ ሙስሊም ነጋዴዎችና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ከጥንት ጀምሮ የሚነግዱበት “ቅዳሜ ገበያ” በጅምላ ነው የወደመው። ከጥቂት ሱቆች ውጭ ሁሉም ከነሙሉ ካፒታሉ ወድሟል፡፡ መንስኤውን እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ብዙ ሱቆች እንደወደሙ ሱቃቸው የተቃጠለባቸው ለቢቢኤን ገለጹ፡፡ በወቅቱ የመጡ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት ዝቅተኛ መሆን እንዳሳዘናቸውና እሳቱን ቶሎ ለመቆጣጠር እንዳልቻለ አስረድተዋል፡፡

ቅዳሜ ገበያ ከዚህ ቀደምም እሳት ሲቃጠል ቶሎ ነበር የሚያጠፉት ያለችው የሱቅ ባለቤት የትላንቱን ግን ቶሎ እንዳልተቆጣጠሩት በመግለጽ ሆን ተብሎ የተደረገ ሳይሆን እንዳልቀረ ግምትዋን ገልፃለች፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው ምናልባትም ሙስሊሞች በኢድ ቀን ባደረጉት ተቃውሞ ምክኒያት ሆን ተብሎ የተደረገ ሳይሆን እንዳልቀረ ገልፀዋል፡፡

Abdurehim Ahmed's photo.
Abdurehim Ahmed's photo.

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE