መሣርያ ለማስፈታት ወደ ወገራና ወደ በለሳ የተንቀሳቀሰው ሁለት ጋንታ የወያኔ ጦር ተደምስሷል።

30 የወያኔ ወታደሮች ሲገደሉ 20 ወታደሮች ተማርከዋል፤

መሣርያ ለማስፈታት ወደ ወገራና ወደ በለሳ የተንቀሳቀሰው ሁለት ጋንታ ጦር የወያኔ ጦር ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2009 ዓም በዐማራ ገበሬ ተደምስሷል።
ከቦታው በስልክ እንዳረጋገጥነው በምዕራብ በለሳ፣ በወገራና በጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች ትጥቅ ለማስፈታት የተንቀሳቀሱ በሁለት ጋንታ የወያኔ ጦር የታቀፋ 30 ወታሬሮች ምንም ሳይተርፉ የተገደሉ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ከሄዱት ከመቶ በላይ ወደሮች ውስጥ 20ዎቹን ማርከናቸዋል ብለዋል። ዐማራው ከየቦታው እየደረሰልን ቢሆንም ለአርማጭሆና ለቋራ ሕዝብ መልእክት አስተላልፉልን ብለዋል።የወገራንና የበለሳን ዐማራ ትጥቅ ለማስፈታት በሁለት ዙር የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ወድሟል። የሞቱ የጠላት ወታደሮች 30 ሲደርስ 15 የተማረኩት በሕይወት በሕዝብ ቁጥጥር ስር ናቸው። ከገበሬዎች በኩል 3 ቆስለዋል። 41 ክላሽና መትረጊስ ተማርኳል።
አመሻሹን ብዛት ያለው የወያኔ ጦር ወደ ቦታው የተንቀሳቀሰ ሲሆን ገበሬዎች ሸሽተን ኃይላችን በማደራጀት ላይ ነን ብለዋል።

የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE