ባህርዳር በአጋዚ ሰራዊት የተገደሉ የጎንደር ልጆች አስክሬናቸው ወደ ጎንደር ሲገባ ታላቅ ቁጣ ይቀሰቀሳል ተብሎ ተፈርቷል፡፡

ጎንደር አራዳ ምድረ ገነት ጃንተከል ዋልታ በታች በዚህ ሰዓት በርካታ ወጣቶች መንገድ ዘግተው በተቃውሞ ላይ ይገኛሉ፡፡

በረከት ስምዖን አዲሱ ለገሰ ጎንደርን ለቃችሁ ውጡ ወያኔ ያፈሰሰው ዳማችንን እንመልሳለን! የትግሬ የበላይነት አንቀበልም! ኮሎኔል ደመቀ ይፈታ! በማለት አገዛዙ አንፈልግም እያሉ በተቃውሞ ላይ መሆናቸው ከጎንደር እየተሰማ ነው፡፡

ለእሮብ በፍርድ ቤት ቀጠሮ ለመገናኘት ሁሉም የጎንደር ወጣት ቀጠሮ ይዟል፡፡ እሁድ እለት ባህርዳር በአጋዚ ሰራዊት የተገደሉ የጎንደር ልጆች አስክሬናቸው ወደ ጎንደር ሲገባ ታላቅ ቁጣ ይቀሰቀሳል ተብሎ ተፈርቷል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE