የግንቦት ሰባቶች በነጻነት ተዋጊነት ስም በኤርትራ በረሃ በቁም እስር አንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል፤በግርግር ስልጣን ለመያዝ መመኘት ኣደጋ ኣለው። (ፈንቅል ኣባቄራ)

  • ከኤርትራ ተነስቼ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻ ኣወጣለሁ ማለት ዘበት መሆኑን ኣሁንም ሊማሩበት ኣልቻሉም
  • ልብ ሊገዙ ኣልቻሉም ሻአቢያ ወያኔ እንደሚወድቅ ካረጋገጠ በሕዝብ ትግል ስም በግርግር ስልጣን ሊያሣጨው ፈልጎም እንዳይመስልህ ሻአቢያ በኣስመራ ያደራጀው የራሱ ስልጣን የሚቆጣጠር ሃዪል ኣለው
  • ይህ ሃይል ግንቦት ሰባትን ሽፋን ኣድርጎ ገብቶ ሳልሳይ ወያኔን ለስልጣን ያበቃል

በቅርቡ ልክ እንደባለፈው ኣይነት የኣርባምንጭ ኣይነት ፌክ ዜና ይሰራና ግንቦት ሰባት ሃላፊነት እንዲወስድ ይደረጋል።ከዛ ስሙን ይጠብቃል።ኣስቂኝ የሆነ ትግል ነው።ግንቦት ሰባት ብሎ ራሱን የሚጠራውና በኤርትራ ምድር መሽጌ ነው ያለሁት የሚለው ወደ ኣስር የሚጠጉ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ የነጻነት ኣርበኞች ኣስመርቄ ዝግጁ ነኝ በማለት ቱሪናፋውን የሚነፋው የብርሃኑ ነጋ ድርጅት ኤርትራ ኣፍንጫ ስር ያለው ጎንደር ሕዝቡ ከሁመራ አስከ ባህርዳር ኣብዮት ኣቀጣጥሎ እየታገለ ባለበት ሰኣት የት እንደገባ ሳይታወቅ ድምጹን ኣጥፍቷል፥ ድርጅቱ ብቻ ሳይሆን ተሳዳቢ ዘርጣጭ እና የፖለቲካ ብስለት የጎደላቸው ኣባላቱም በእንፉቅቅ ላይ ሆነው ስለ ጎንደር እና ጎዣም ዥግነንት ሊሰብኩን ይሞክራሉ።

እንደ መንፈስ ቅዱስ የትም ቦታ ብትሆኑ በመካከላችሁ አለን የምትል ኣዲስ የፖለቲካ መሸወጃ ያነገቡት ግንቦት ሰባቶች በሁሉም ቦታ አለን፣በመካከላችሁ ነን ምናምን ብትሉ በጣም ስለሚያሳፍር አርፋችሁ ቁጭ በሉ።ጉድ እኮ ነው መንፈስ ቅዱስ ነው እንዴ ግንቦት ሰባት መካከላችሁ ነን እያላችሁ ህዝቡን አደነዘዛችሁት። የወያኔ ኣባት የሆነው ሻእቢያ ጉያ ስር ተወሽቀው በኢሳያስ ኣፈወርቂ ትእዛዝ የሚሾሩት ግንቦት ሰባቶች በሕዝብ መካከል እንዳሌሉ ብዙ ማረጋገጫዎች እና የትግሉ ኣክቲቭስቶች መረጃዎች በጃቸው ኣለ፤ ሃገር ቤት ያለውን የሰላማዊ ትግል እና የሕዝብን እንቅስቃሴ በማጣጣል ራሳቸውን በመስቀል በወያኔ ሻእቢያ የፕሮፓጋንዳ ጡዘት ትቦ ውስጥ የሚንደፋደፉት ግንቦት ሰባቶች በሻእቢያና ወያኔ ድብቅ ሴራ በወሬ ብቻ ተጠምደው ሕዝብን ለማደንዘዝ እና በነጻነት ተዋጊነት ስም በ ኤርትራ በረሃ በቁም እስር አንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል።

ከኤርትራ ተነስቼ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻ ኣወጣለሁ ማለት ዘበት መሆኑን ኣሁንም ሊማሩበት ኣልቻሉም።ልብ ሊገዙ ኣልቻሉም ሻአቢያ ወያኔ እንደሚወድቅ ካረጋገጠ በሕዝብ ትግል ስም በግርግር ስልጣን ሊያሣጨው ፈልጎም እንዳይመስልህ ሻአቢያ በኣስመራ ያደራጀው የራሱ ስልጣን የሚቆጣጠር ሃዪል ኣለው ይህ ሃይል ግንቦት ሰባትን ሽፋን ኣድርጎ ገብቶ ሳልሳይ ወያኔን ለስልጣን ያበቃል፥እንጂ ሻአቢያ ግንቦት ሰባትን በዚህ ቀውጢ ሰኣት ሂዱና ሕዝብን ኣግዙ ብሎ በፍጹም ኣይልካቸውም።ኣያደርገውም ከልጁ ከወያኔ የሚበልጥበት የለም። በቅርቡ ልክ እንደባለፈው ኣይነት የኣርባምንጭ ኣይነት ፌክ ዜና ይሰራና ግንቦት ሰባት ሃላፊነት እንዲወስድ ይደረጋል።ከዛ ስሙን ይጠብቃል።ኣስቂኝ የሆነ ትግል ነው።

በኢሳት ስር የሚገኙ ጋዜጤኞችና ያደሯጇቸው የማህበራዊ ድህረገጽ ተሳዳሚ ኣሽከሮቻቸው በቅርቡ የግንቦት ሰባት ኣባል ያልሆኑ ኣክቲቭስቶች ላይ ወያኔ የሚል ስም እየለጠፉ የስድብ ጅራፎቻቸውን ያጮኻሉ ተብሎ ይጠበቃል።ግንቦት ሰባት ሕዝቡ የተቆጣጠራቸውን ከተሞች ዘልቆ ገብቶ በመረከብ ከሕዝቡ ጋር መታገል ሲገባው የሃሰት ዜና እያራገበ የዲያስፖራውን ኪስ ያጥባል፤ ዲያስፖራው ለ ኤርትራ የውጪ ምንዛሬ ኣንደኛው ኣካል ከሆነ ቆየ፥በትግል ስም የሚሰበሰቡ ዶላሮች ወደ ኣስመራ መንግስት ካዝና ይዘልቃሉ። ኣሁንም መንቃት ኣለብን ወያኔ የሻእቢያ መንግስት ተላላኪዎች እያለ የሚያራግበው ነገር ሁሉ ሃሰት ነው ወያኔ ራሱ እስካሁን ደቂቃና ሰከንድ የሻእቢያ መግስት ተላላኪ መሆኑ እየታወቅ ሕዝቡን በማደንዘዝ ተግባር ላይ የተሰማራ ሲሆን ከነጻነት ታጋይነት ወደ መንፈስ ቅዱስነት የተዘዋወረው ግንቦት ሰባትም ሌላኛው ኣደንዛዥ ሃሰተኛ መሆኑን ልንነቃ ይገባል፥፥የሕዝብ ትግል ኣይሞትም፥በግርግር ስልጣን ለመያዝ መመኘት ኣደጋ ኣለው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE