የንጉስና የዘውድ ስልጣን ለዜጋዎች እንደ መስጠት ለጎሳ የዘር መሳፍንቶች ስለሰጠ።
የዘውድና ባላባቶች ግላዊ ንብረት የነበረው የኢትዮጵያ ምድር፣ እግዚአብሄር የፈጠረው የኢትዮጵያ መሬት ነጻ አውጪ ለሚባሉ የጎሳ መሳፍንት ግላዊ ንብረት በማድረግ የኦሮሞ መሬት፣ የአማራ መሬት፣ የትግሬ መሬት ወዘተ ብሎ መሬት ላራሹ የሚለው ፍትሃዊ ጥያቄን ጠልፎ የጎሳ ሌቦችና ግፈኞች መፈልፈያ ቆሻሻ የጦርነትና ቀውስ ረግረግ ስለፈጠረ።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ምን ግዜም ለማያበቃው የጎሳና ጎሳ ጦርነት መፍለቂያ ቆሻሻ ረግረግ፣ ኢትዮጵያን አለ ጥርጥር የሚደመስሰው የጎሳ መሬት ጥያቄ ነው። አብዮቱ መሬት ለአራሹ አልሰጠም ።
የመሬት ጥያቄ በብሄር ጥያቄ ተጠልፎ መሬት ላራሹ ለግለሰብ ገበሬ ሳይሆን መሬት ለመንግስት በመስጠት አዲስ የጎሳ ፊውዳሊዝም መሰረተ ።
የጎሳ መንግስት የመሬት ባለቤት ሆኖ ዛሬ ያለው አለምንም ጥርጥር የጎሳ ፊውዳሊዝም ነው።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ አንዴ በትግሬ፣ አንዴ በኦሮሞ፣ አንዴ ባማራ፣ አንዴ በሱማሌ፣ አንዴ በመተከል እያለ የሚፈነዳው የጎሳዎች የመሬት ጦርነት የጎሳ ፊውዳሊዝም እና የጎሳ መሬት ባለቤትነ ጥያቄ እስካልፈረሰ ድረስ በኢትዮጵያ ዕከልዊ መንግስት አይጸናም።
አሁን ይደረጋል የሚባለው እድገት ብልጽኛም መሰረተ ቢስ የጎሳዎች መተላለቂያ፣ መጠፋፊያ አዲሱ የጎሳ ፊውዳሊዝም፣ የጎሳ ይገባኛል የጎሳ ዘመን መሳፍንት የማያባራ እርስ በርስ ጦርነት ነው ።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሃይማኖት ግጭቶች የሚባሉት በጎሳ መንግስትና በሙስሊሞች፣ በጎሳ መንግስትና በኦርቶዶክክስ መሃል ያለውና የሚኖረው ትግልና ጦርነት ሁሉ ዋና መነሾው የመሬት ጥያቄ ነው፣ የጎሳ ፊውዳሊዝም ያመጣው በአንድ ጎሳ የመሬት ቁጥጥርና ባለቤትነት ነው ።
የቀራንዮ ክርስቲያኖች ደም የፈሰሰው በመሬት የጎሳ ፊውዳል መሳፍንቶች ፣ በጎሳ የመሬት ነጋዴዎች እጅ ነው።
አንድም የኢትዮጵያ ጎሳ ወይ ክላን የኢትዮጵያን መሬት አልፈጠረም! አንድም ጎሳ ይህ አገር የኔ ንብረት ነው፣ ይህ መሬት የኔ ጎሳ ሃብት ነው የማለት መብት የለውም ! ይህ ነው የጎሳ ፊውዳሊዝም ማለት ።
የትግሬ ጎሳ መሳፍንት ባረቀቁት ሕግና በነደፉት ባንዲራ ተሸፋፍኖ አዲስ ሊቦካ የሚሞከረው ብልጽግ ና በሚባል የዳቦ ስም የሚሞካሸው አዲሱ የጎሳ ፊውዳሊዝም ምንነት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በቶሎ እንዲቃወሙት እንዲያፈርሱት ግድ ይላል ።
ከ1966 ጀምሮ የሆነው ባጭሩ ይህ ነው ፤ መለኮታዊ ንጉሳዊ የዘውድ አገዛዝ በጎሳ በዘር መለኮታዊ አገዛዝ ተለወጠ። የንጉስ ዘር ስልጣን ከመለኮት ተገኘ ይባል ነበር ።
ዛሬ የጎሳ ዘር ስልጣንም ያው ምንጩ መለኮት ነው ። አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰው፣ ህጋዊ ሰው ሳይሆን መለኮታዊ ጎሳ፣ መለኮታዊ ዘር ነው ። የጎሳ ዘር እግዚአብሄርን የሰራውን መሬት በጎሳ ፊውዳላዊ ክብረ ጎሳ ድንጋጌ የመሬት ባለቤት፣ የመንግስት ባለቤት፣ የኢኮኖሚ ማናምን እድገት ፎጋሪ ሆኖዋል።
ጎሳ ኢኮኖሚ አይገነባም፣ ግለሰቦች፣ ዘመናዊ ህዝቦች ናችው የስልጣኔ ፈጣሪዎች!!
ይህ ጸረ ጎሳ ፊውዳሊዝም ትግል ዛሬ መከሰቻው በመሬት ጥያቄ፣ በመንግስት ስልጣን እና በሰንደቅ አላማ ጥያቄ ላይ ተወጥሮ ይገኛል። ይህ ውጥረት የጎሳ ፊውዳሊም እስካለ ድረስ ፣ የጎሳ መሬት እስካለ ድረስ፣ የትግሬ ጎሳ ሰንደቅ እስካለ ደስ መላላት ሳይሆን እየተወጠረ ይሄዳል።
በ50 አመታት ትግል ያተረፍነው የዘውድ አገዛዝ በጎሳ አገዛዝ መተካቱ፣ የፊውዳል ባላባቶች መሬር ወደ ጎሳ መሳፍንቶች ባለቤትነት መሸጋገሩ እና የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ መለያ በትግሬ ፔንታግራም ትርጉም የለሽ ምልክት መተካቱ ነው ።
ይህም በመሆኑ ኢትዮጵያ ለማያቋርጥ የዘር እና የሃይማኖት ጦርነት ተዳርጋ አለች !
ያለው መውጫ አንድ ቀዳዳ፣ አንድ መስኮት ነው ፤ የጎሳ ፊውዳሊአምን ማፍረስ፤ ያም ማለት ክልልና ያንድ ጎሳ መንግስት፣ ያም ማለት የጎሳ ኢኮኖሚ ብልጽኛ የሚባል ዘመናዊ ፊውዳል ስርዓትን ከስሩ መንቀል ነው ። ያ ሳይሆን ኢትዮጵያ የትም ፈቀቅ አትልም።
ሆረስ ነኝ