Page 1 of 1

የሕዳሴው ግድብ የዲሲ ስብሰባ በስድስት ነጥቦች ላይ ከስምምነት ደረሰ፤ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ አይበጅም ተብሏል።

Posted: 16 Jan 2020, 03:03
by MINILIK SALSAWI
የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው ዝርዝር መሰረት ኢትዮጵያ ግድቡን በሐምሌና ነሐሴ በዓመት ሁለት ጊዜ ትሞላለች። ለዓስር ወር ውሐ በግድቡ ሳይሞላ ለግብጽ ይለቀቃል ማለት ነው። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በስፋት የውይይቱን በሰላም መጠናቀቅ ቢዘግቡም የሆነው ግን በተቃራኒ በመሆኑ የግድቡ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ኢትዮጵያን የሚጎዳ ስምምነት እንዳይፀድቅ የገለጹት ስጋታቸው እውን መሆኑ እየታየ ነው። አስተያየት ሰጪዎች የስምምነቱ ዝርዝር በባለሙያዎች ማብራሪያ እንዲሰጥበት እየጠየቁ ነው።

Joint Statement of Egypt, Ethiopia, Sudan, the United States and the World Bank
https://mereja.com/amharic/v2/201344