Minilik Salsawi በሙላቱ ተሾመ ስም አልጀዚራ ላይ የጻፈው አብይ አሕመድ ኤርትራ ላይ ያቀደውን እየነገረን ነው። ……. አንዲትን ሉዐላዊ አገር ለመድፈር ሲባል ብቻ ትላንት ባለውለታ የጨለማ ጊዜ ወዳጅ እያለ ትግራይን ያዘረፈና ያስወረረ አካል ዛሬ ላይ በክህደት ቢናውዝ ካለፈው በመረዳት ሊደንቀን አይገባም። ……. ኢሳያስ ምንም አምባገነን እና ፀረ ኢትዮጵያ ቢሆንም የአብይን የጦርነት እቅድ መደገፍ ግን እብደት ነው። ……… ትላንት ቀለበት አስሮ ዛሬ ተፋቶ ነገ ጦር መስበቅ ተቀባይነት የለውም። አብይ አሕመድ በሙላቱ ተሾመ ስም አልጀዚራ ላይ የፃፈውእጅግ አደገኛ አካሄድ ሊጤን እና ሊመረመር ይገባል። ሙላቱ ተሾመ ካለው ማንነት አንፃር ሲመዘን እንደዚ አይነት መረን ፅሁፍ ደፍሮ በፍፁም አይፅፍም። …….. በሶማሊያ አሸናፊት የደረሰውን የዲፕሎማሲ ውድቀት አለመማር ድንቁርና ነው። ………… ጦርነትን እንደ አንድ ዋነኛ የፖለቲካ ስልጣን ማስጠበቂያ አድርጎ የሚያስበው የአብይ አሕመድ አገዛዝ ኤርትራ ላይ ጦርነት ለመክፈት የሚያስችሉትን መንደርደሪያዎች መጎሰም ከጀመረ ሰነባብቷል። ……… ካሁን በኃላ ጦርነት ለማድረግ ለስልጣን እርዝማኔ ሲባል ብቻ …. ” በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ሽፋን ማጭበርበር አይቻልም። የጦርነት እልቂት ይብቃ ! #MinilikSalsawi
