የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ዕዝ ካምፖች እንዲሠፍር ፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ እንዳስተላለፈ ተደርጎ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተሠራጩ መረጃዎች ስህተት ናቸው አለ። ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ መከላከያ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ በሚገኝ የቀድሞ ካምፖቹ እንዲሠፍር ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስምምነቱን ገልጧል ተብሎ የተሠራጨው መረጃም ሐሰት ነው ሲል አስተባብሏል። መረጃዎቹ “የተሳሳቱ”፣ “ሕዝብን ለማወናበድ የታለሙ” እና “አላስፈላጊ ውጥረት ለመፍጠር የታሰቡ” ናቸው ያለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የመረጃዎቹ “ምንጭም” ሆነ መረጃዎቹ እንዲያሳኩት የተፈለገው “ግብ” ግልጽ ነው ብሏል። በተዛማጅ ዜና፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የጦርነት ትርፉ “ሞት”፣ “ጥፋት”፣ “መፈናቀል” እና “ረሃብ” እንደሆነ በመግለጽ፣ ለልዩነቶች ሁሌም “ፖለቲካዊ መፍትሄ” እንዳለና ለሰላም ዕድል መስጠት እንደሚያስፈልግ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።🕊️