አባናደው ክፍለጦር በሁለት አውደ ግንባሮች ባደረገው ተጋድሎ 29 የአገዛዙ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጉ ታወቀ!

አባናደው ክፍለጦር በሁለት አውደ ግንባሮች ባደረገው ተጋድሎ 29 የአገዛዙ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጉ ታወቀ!

በነዚህ ሁለት ግንባሮች ላይ በተደረገ ውጊያ ከተገደሉ ወታደሮች በተጨማሪ የቆሰሉ ወታደሮችን የገዛ ጓዶቻቸው ትጥቃቸውን ገፈው ጥለዋቸው ሄደዋል።

በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አባናደው ክፍለጦር ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረገው ተጋድሎ የጠላት አከርካሪን በመስበር አንፀባራቂ ድል መቀዳጀቱን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ተጋድሎው የተደረገው በምስራቅ አማራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች መካከል አንዷ በሆነችው ከላላ ወረዳ ልዩ ስሙ ባከት ተብሎ በሚጠራው አከባቢና ሻፊ ላይ ነው።

የመጀመሪያው ውጊያ በከላላ ወረዳ ልዩ ስሙ ባከት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲሆን በዚህ ግንባር ለተከታታይ 8:00 ሰዓታት ከባድ የሆነ የጨበጣ ውጊያ መደረጉን ክፍለጦሩ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

በውጊያው ሰባት የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ 15 ወታደሮች ደግሞ ክፉኛ ቆስለው በሞትና በሕይወት መካከል ይገኛሉ።

በዚህ ግንባር በተደረገ ውጊያ ከተገደሉ ሰባት ወታደሮች በተጨማሪ የቆሰሉ 15 ወታደሮችን የገዛ ጓዶቻቸው ትጥቃቸውን ገፈው በአከባቢው ጎራዴ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ጥለዋቸው መሄዳቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

በአውደ ግንባሩ ከዙ23 ጀምሮ ሌሎች ከባባድ መሣሪያዎችን ታጥቆ ለወረራ ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ ጥቃት በመክፈት
ድል የተቀዳጁት በአባናደው ክፍለጦር ስር ከመሀመድ ዳውድ ሬጅመንት የተወጣጡ የፋኖ አባላት ናቸው።

በተመሣሣይ በቀጥናው ሻፊ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአባናደው ክፍለጦር ስር የሸዋንግዛው ሬጅመንት አባላት ባደረጉት ተጋድሎ ከሰባት ወታደሮች በላይ ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን በርካታ የጠላት ወታደራዊ ንብረቶችም በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።