ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወታደሮቻቸውንና ጦር መሳሪያዎችን በትግራይ አካባቢ እያከማቹ መሆኑን ከቀጠናው ዲፕሎማቶች መስማቱን ጠቅሶ ብሉምበርግ ዘገበ። የኢትዮጵያ ወታደሮችና ጦር መሳሪያዎች በባሕርዳር በኩል ወደ ሰሜን አቅጣጫ መጓዛቸውን ምንጮች እንደነገሩት የዜና ምንጩ ጠቅሷል። የኤርትራ ወታደሮችም ወደ ትግራይ የተለያዩ ቦታዎች ዘልቀው መግባታቸውን መረዳቱን የዜና ምንጩ አመልክቷል። የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል፣ ‘ኢትዮጵያ ራሷ የምትቆጣጠረው የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ዓለማቀፍ ድጋፍ የለውም’ በማለት ነግረውኛል ሲል ብሉምበርግ በዚሁ ዘገባው ላይ ጠቅሷል።