የእስራኤል ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተነገረ

የእስራኤል ፕሬዝዳንት ይስሃቅ ሄርዞግ፣ በቀጣዩ ሳምንት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተነገረ። ፕሬዝዳንት ሄርዞግ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የአንድ ቀን ጉብኝት፣ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ አንድ የእስራኤል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ነግረውኛል ሲል ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ጋዜጣ ዘግቧል። የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት እስራኤል ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የያዘችው እቅድ አካል እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ፕሬዝዳንት ሄርዞግ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ የተያዘ እቅድ ስለመኖሩ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው ነገር የለም። የቀድሞው የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሪዩቨን ሪቭሊን ከሰባት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው አይዘነጋም።