በኢትዮጵያ መንግሥት፣ በትግራይና በኤርትራ መካከል ውጥረት በሱዳን ከሚካሄደው ግጭት ጋር ተዳምሮ ኃያላን አገራትን ወደ ግጭቱ ሊስብ እንደሚችል ተጠቆመ

ዓለማቀፉ የግጭት አጥኝ ቡድን (ክራይስስ ግሩፕ)፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት፣ በትግራይና በኤርትራ መካከል ውጥረት በመባባሱ በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ በቀጠናው ጦርነት ሊከሠት ይችላል ሲል ስጋቱን ገለጠ። ተቋሙ፣ በቅርቡ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በድሮን ጭምር የተካሄደው ግጭት፣ ኤርትራን ጭምር ጎትቶ በማስገባት ሠፊ ጦርነት ሊያስክትል እንደሚችል ገልጧል። በሰሜን ኢትዮጵያ አዲስ ግጭት ከተቀሠቀሠ፣ በሱዳን ከሚካሄደው ግጭት ጋር ተዳምሮ ኃያላን አገራትን ወደ ግጭቱ ሊስብ እንደሚችል የጠቆመው ተቋሙ፣ ተለዋዋጩን የቀይ ባሕር ቀጠና ጭምር የሜወክ እድል አለው ሲል አስጠንቅቋል። ተቋሙ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የአፍሪካ አገራት እና ዓለማቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያ መንግሥትንና ሕወሓትን እንዲያሸማግሉም ጠይቋል።

 ….. https://miniliksalsawi.substack.com/p/tensions-are-running-high-among-the  ……