ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 15 ሚሊዮን ዶላር መለገሷን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለሱዳኑ ጦርነት ተጎጂዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማሰባሰብና የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገ ከፍተኛ ጉባኤ ላይ አስታውቀዋል።
ጉባኤውን በትብብር ያዘጋጁት፣ ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ ናቸው።
ዐቢይ፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ለሱዳን ዘላቂ ሰላም መስፈን እንዲሠራና ተፋላሚ ኅይሎች ለሰላማዊ መፍትሄ እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሱዳን፣ ኢምሬቶች የገባኤው አስተባባሪ መኾኗን ቀደም ብላ ተቃውማ ነበር።