የአየር መቃዎሚያ ጭምር ታጥቆ ሲንቀሳቀስ በነበረ የአገዛዙ ኃይል ላይ በተፈፀመ ሽምቅ ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!
በምዕራብ አማራ ቀጠና ሁለት እጁነሴ ወረዳ ልዩ ስሙ አጋም ውሀ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ዛሬ የካቲት 10/2018 ዓ/ም ማለዳ በተፈፀመ የሽምቅ ጥቃት በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
የአየር መቃዎሚያ(ዙ23)ን ጨምሮ በሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች ሽፋን የታገዘ በርካታ የጠላት ብልፅግና ወታደራዊ ኃይል መነሻውን ከሞጣ በማድረግ በአከባቢው ሲንቀሳቀስ ልዩ ስሙ አጋም ውሃ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ ነው ሊመከት የማይችል ከባድ የሽምቅ ጥቃት የተፈፀመበት።
ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራ የተከናነበው የጠላት ኃይል፡ አስከሬን ለመሰብሰብ በሚል በአጋም ውሀ አከባቢ ባሉ ተራራማ ስፍራዎች ላይ የዘፈቀደ ድብደባ በመፈፀም የአርሶ አደሮችን ሀብት ንብረት አውድሟል።
በጠላት ላይ የተጠናና ሊመከት የማይችለውን የሽምቅ ጥቃት በመፈፀም በርካታ ወታደሮችን በመደምሰስ ድል የተቀዳጁት በአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የሚገኙ ፋኖዎች መሆናቸውንም ነው ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።