ዐብይ አህመድ ዛሬም በንፁኋኖች ላይ የሚፈፅነው የድሮን ጥቃት ተባብሶ ቀጥሏል።
የካቲት 10/2018 ዓ/ም በሸዋ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የድሮን ቅኝት ሲደረግ ያረፈደ ሲሆን፡ ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በቀወት ወረዳ አያበር ቀበሌ ጤና ጣቢያ ላይ ጥቃት ተፈፅሟል።
በጥቃቱ ሶስት ንፁኃን ሲገደሉ ቀጥራቸው አምስት (5) የሚሆኑ ንፁኋን ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። ከጥቃቱ ሰለባዎች መካከል ሴቶችና ህፃናት ይገኙበታል።
በውድቀት ዋዜማው ላይ መሆኑን በመረዳት ተስፋ የቆረጠው የፋሽቱ አብይ አህመድ አገዛዝ ሰሞኑን በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከሰሞኑ በበርካታ ቦታዎች ሽንፈት የተከናነበ ሲሆን የጀግኖቹን በትር መቋቋም አልችል ብሎ የእውር ድንብር የሚያደርገው እንቅስቃሴ በማቆም ከተማ ተፋስስ ውስጥ ተወሽቆ ያለ ቢሆንም የበቀል ጥማቱን ለመወጣት ንፁሐኖችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየፈፀመ ነው።
በዛሬው ዕለት ማለትም የካቲት 10/06/2018 ዓ.ም በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በቀወት ወረዳ አያበር ቀበሌ ጤና ጣቢያ ላይ የተፈፀመው የድሮን ጥቃት ምንም አይነት የፋኖ ሰራዊት አባላት በሌለበት፣ውጊያ በሌለበት ፣ ሴቶችና ህፃናት በሚገኙበት ጤና ጣቢያ ላይ በጭካኔ በተወረወረ የድሮን ቅንቡላ ንፁሃኖች ሠለባ ሆነዋል።
በህዝብ ስም እየተበደረ ያመጣውን የድሮን ቅንቡላ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ ንፁሃን ላይ በዘፈቀደ እየወረወረ ያለው ፋሽታዊው አገዛዝ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የተለያዩ ቀጠናዎች ተደጋጋሚ የድሮን አሰሳ እያደረገ ስለሆነ ህዝባችን እና ሠራዊታችን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን እንጠብቅ።
ምንጭ፦ ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ክፍል!!