ተጠባባቂ ኃይል ማስመረቁን በመካነሰላም ግንባር የሚንቀሳቀሰው ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ገለፀ!!

ተጠባባቂ ኃይል ማስመረቁን በመካነሰላም ግንባር የሚንቀሳቀሰው ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ገለፀ!!

የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ከሚኖሩ የግል ታጣቂዎች መካከል ፍቃደኛ የሆኑትን በመመልመል ወታደራዊ እና የፓለቲካ ስልጠና እንድወስዱ በማድረግ በተጠባባቂ ኃይልነት ማስመረቁ ታውቋል::

የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እና ኢትዮጵያም እንደ ሀገር ፀንታ እንድትኖር ለማስቻል የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ተጠባባቂ ኃይልን ለመቀላቀል ወስነው ስልጠናውን መውሰዳቸውን የገለፁት ተመራቂዎች በመካነሰላም ግንባር ብቻ የተፈፀመው የግፍ ግፍ እኛ ቤት እንዳንውል የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል:: ተመራቂዎች አክለውም የተጀመረው የህልውና ትግል ፅናትን እንደሚጠይቅ እናውቃለን ያሉ ሲሆን ጠብመንጃ የነከሱበትን ወርቃማ አላማ ሁሌም እያስታወሱ በፅናት እና በጀግንነት ለአማራ ህዝብ ዘብ እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል:: ነፃነት በነፃ ስለማይገኝ ሁሉም አማራ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም ነው ተመራቂዎች የገለፁት::

የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ኮማንዶ ጀንበሩ ጌታቸው እና የክፍለ ጦሩ አባል የሆነው ኮማንዶ ጠለለው አሰፌ እንድሁም የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኦርድናንስ አርበኛ በፍቃዱ ገንብር ከምኒልክ ዕዝ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ጋር በመተባበር ወታደራዊ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን የተጠባባቂ ኃይሉ አባላትን የፓለቲካ ንቃተ ህሊና ለማሳደግ የሚያስችላቸው ስልጠና ደግሞ ከዕዙ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በመጣ አካል እንድሰጥ ተደርጓል::
©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!