ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ)፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ያገዱትን የሮይተርስ ዜና ወኪል ሦስት ጋዜጠኞች የሥራ ፍቃድ እንዲመልሱ ጠየቀ።

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ)፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ያገዱትን የሮይተርስ ዜና ወኪል ሦስት ጋዜጠኞች የሥራ ፍቃድ እንዲመልሱ ጠየቀ።

ሲፒጄ፣ መንግሥት ሮይተርስ ላይ የወሠደው ርምጃ፣ በዓለማቀፍ እና ነጻ መገናኛ ብዙኀን ላይ ሲወስድ የቆየው “አፋኝ ርምጃ” ቀጣይ ነው በማለት ተችቷል።

የሮይተርስ ጋዜጠኞች ፍቃድ እና ዜና ወኪሉ በአዲስ አበባ ከቀናት በፊት የተካሄደውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ እንዲዘግብ የተሠጠው ፍቃድ የተነጠቀው፣ ኢትዮጵያ ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወታደራዊ ማሠልጠኛ አቋቁማለች በማለት ሮይተርስ የምርመራ ዘገባ በመስራቱ እንደሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዘኀን ባለስልጣን “ይፋዊ ባልሆነ መንገድ” ጠቁሟል ሲል የዜና ወኪሉ ቀደም ሲል ገልጦ ነበር።

የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሙቶኪ ሙሞ፣ ባለሥልጣናት በሌሎች መገናኛ ብዙኀን ላይ የጣሏቸውን ገደቦች እንዲያነሱና ነጻ ጋዜጠኝነትን እንደ ስጋት ማየት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።