የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የትግራይ ሕዝብ ከእንግዲህ “ጭቆና” እና “ግፍ” ፈጽሞ እንደማይቀበል ማረጋገጥ እንፈልጋለን አለ።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የትግራይ ሕዝብ ከእንግዲህ “ጭቆና” እና “ግፍ” ፈጽሞ እንደማይቀበል ማረጋገጥ እንፈልጋለን አለ።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው፣ “ብሄራዊ አንድነት የራስን እድል በራስ የመወሠን መብትን ለማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን ሕወሃት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 51ኛ ዓመት በዓል አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የትግራይ ሕዝብ የታገለለት ሰላም እና በትግሉ የገነባው ፌደራላዊ ሥርዓት አደጋ ላይ ወድቀዋል ብሏል።

የትግራይ ሕዝብ፣ የትግራይን ግዛታዊ አንድነት ለማረጋገጥ፣ የታጠቁ ኃይሎችን ከትግራይ ለማስወጣት፣ ተፈናቃዮች ደኅንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል እንዲሁም የግጭት ማቆም ስምምነቱ “ሙሉ በሙሉ” እና “ሊረጋገጥ በሚችል” መልኩ እንዲተገበር እንዲታገልም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥሪ አድርጓል።