“ልፋፈ ጽድቅ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ልፋፈ ጽድቅ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ባለፈው ሳምንት “ኢትዮጵያን ትፏት” ላሉት ለአባ ሠረቀ ወ/ሳሙኤል ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የጻፏትን ጦማር አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ ቀሲስ አስተርአየ ተዝቆ ከማያልቀው ዕውቀታቸውና ክህሎታቸው ቆንጠር አድርገው  በተለያዩ ርዕሶች ካዘጋጇቸውና ከሰበሰብናቸው ጦማሮች መካከል ለፓትርያርኩ የጻፏትን አገኘን፡፡ በጦማሯ የተላለፈው መልእክት ከ70 ሚሊዮን በላይ ከሚቆጠረው ምዕመናን በበለጠ ሁኔታ ጳጳሶችን፣ ቄሶችንና ሰባኪዎችን ወደ የሕሊናቸው እንዲመለሱ እንደሚረዳቸው ጥርጥር የለውም፡፡

ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን በቀኖናዋና በስነ መለኮት አተረጓጎሟ ሳትወሰን በአልባሳቱም የምታስተምርበትን ሳይማሩና ሳይረዱ በቤተ ክህነቱ የተሰገሰጉት ቁጥራቸው እንደበዛ የታወቀ ነው፡፡ globalization ጎትቶ ባመጣቸው በተለየያዩ የሃይማኖት ትምህርቶች ጭንቅላታቸው የዞረባቸውና የተምታታባቸው ዘመናውያን ነጋዴ ሰባኪዎች ሊቃውንቱ ተለይተው ይጠሩባቸው የነበሩትን የማዕረግና የክብር ስሞች ላይ ዓላማዊ ደረጃዎችን እንደ ዶክተርነትና ፕሮፌሰርነት ሳይቀሩ ደራርበው ተሸክመው ሕዝበ ክርስቲያኑን በማመስ ላይ ናቸው፡፡“ከመጠምጠም መማር ይቅደም” የሚባለውን ለዘመናት በቤተክርስቲያኒቷ ሲሰራበት የነበረውና በቤተርስቲያኒቱ አስተምሮ የመጠቁና የላቁ ሊቃውንት እንኳን ማዕረግ ሲሰጣቸው “አይገባንም እያሉ” ይሸሹ የነበረበት መልካም ዘመን አልፎ ሁለት መስመር እንኳን ቅኔ መቋጠርና መቀኘት የማይችለው ግብስብስ ሁሉ በካባ ተኮፍሶ ቤተ ክርቲያንን እንደ ምስጥ እየበላት ነው።

ብዙ የተደራረቡ ሹመቶች ከተሸከሙት ከፓትርያርኩ ጀምሮ ከራሳቸው እስከ እግር ጣቶቻቸው የተጠቀለሉባቸውን የአልባሳት ትርጉም ሳይረዱ ወደ ኃላፊነቱ ለመጡት ሁሉ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ “ልፋፈ ጽድቅ” በሚል ርዕስ ቀሲስ አስተርአየ ያቀረቧትን ጦማር አቀረብንላችሁ ፡፡ በተለይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ ቀሳውስትና ሰባኪዎች አንብቧት፣ ተረዷት እራሳቹህንም ታዘቡባት፡፡ ልፋፈ ጽድቅ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ